top of page
Search

ዩናይትድ ቤቭሬጅ አ.ማ ለሞጆ ከተማ አስተዳደር የሞተር ሳይክሎች ድጋፍ አደረገ!

ዩናይትድ ቤቭሬጅ አ.ማ ለሞጆ ከተማ አስተዳደር ከ250 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገባችው ሁለት ሞተር ሳይክሎችን፤ የሞጆ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ ከድጃ ጀማል፤ የዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘካርያስ ወሊቃ እንዲሁም ሌሎች የሞጆ ከተማ አስተዳደርና የዩናይትድ ቤቨሬጅስ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም በዩናይትድ ቤቨሬጅስ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተከናወነ ስነ-ስረዓት ርክክብ አደረገ።


በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ ከድጃ ጀማል፣ ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ ከተቋቋመ አጭር ጊዜው ቢሆንም ለአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም ለከተማ አስተዳደሩ በሚያደርገው ተከታታይ ድጋፍ በቀዳሚነት እንደምሳሌ የሚጠቀስ ድርጅት ነው ብለው፤ አሁን የተደረገው ድጋፍም የከተማ አስተዳደሩ ያለበትን የትራንስፖርት ቸግር ያቃልላል ብለዋል። የዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘካርያስ ወሊቃ እንደዚሁ፣ ዩናይትድ ቤቨሬጅስ ከምስረታው ጀምሮ ተፈናቃዮችን በማቋቋም፣ በኮቪድ19 ለተቸገሩ የሞጆና አካባቢው አቅመ ደካሞች 1.2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የምግብ እህሎችን በመደገፍ፣ ለ286 ቤተሰቦች አመታዊ የጤና መድኅን ክፍያቸውን በመሸፈን፣ ለ2000 አቅመደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶች በማሟላት፤ ከ200 በላይ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር፤ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጽ/ቤት ህንጻ በማስገንባት እስካሁን ያሳየውን አብሮነት ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ አሁን የተደረገው ድጋፍም

የከተማ አስተዳደሩን ያለበትን የትራንስፖርት ችግር ይቀርፋል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።






30 views0 comments
bottom of page