top of page
Search

ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ ምርት የሆነው ተወዳጁ አንበሳ ቢራ የሞጆና አካባቢዋ ፍሬዎች የሆኑትን የኢፈቦሩ ማኅበር አባላትን ድጋፍ ሰጠ




ኢፈቦሩ በሚል በሞጆ ከተማ አስተዳደር የተደራጁት ከ90 በላይ የሞጆና አካባቢዋ ወጣቶች በድርጅታችን ውስጥ በተለያየ የስራ ክፍል ውስጥ በጫኝና አውራጅነት፣ በፅዳትና ልዩ ልዩ መደቦች እየሰሩ የሚገኙ ናቸው። ድርጅታችን ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማህበርም በመደጋገፍ አንበሳዊ ባህሉ እነዚህን ወጣቶች በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግና ተጨማሪ ገቢ የሚፈጥር የተሟላ የንግድ ቤትና ቁሳቁሶች አሟልቶ እንዲሰሩበት እና ራሳቸውን እንዲያለሙበት አስረክቧል።

ድርጅታችን ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ እንዲህ ላለው የማህበረሰብ ድጋፍ አዲስ አይደለም። ቀደም ሲልም፤

- ለኮቪድ19 ተፅዕኖ መቋቋሚያ የሚሆን ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል

- 1.5 ሚሊዮን ብር በመመደብ ለሞጆ ከተማ አስተዳደር የኮምዩኒቲ ፖሊሲንግ ቢሮ በመገንባት ላይ እንገኛለን

- ለሞጆ ከተማ ተማሪዎችም እንዲሁ ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የትምህርት ቁሳቁሶችን አበርክቷል፤

ለኢፈቦሩ የምናስረክበው ይሄ የተሟላ የንግድ ቤት ለማህበሩ አባላት ካለው ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ በተጨማሪ ሌሎች ወጣቶችን በቋሚ ሰራተኝነት ቀጥረው ተጨማሪ የስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል። ይህም በከተማችን ያለውን የስራ አጥነት ችግር በተወሰነ መልኩ የሚቀንስ እንደሆነ እናምናለን። ወደፊትም የሞጆ ከተማና አካባቢዋን ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራት ላይ አቅማችን በፈቀደው ሁሉ የተለመደ አንበሳዊ ትብብራችንን የምንቀጥል መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

68 views0 comments
bottom of page