ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አክሲዮን ማኅበር የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱና በታማኝነት በመክፈል ከ35 ከፍተኛ ግብር ከፋዮች አንዱ ሆኖ በወርቅ ደረጃ ተሸልሟል። ይህ ሽልማት ለድርጅታችን የተበረከተው፣ የኢፌዴሪ የገቢዎች ሚኒስቴር “ግብር ለሀገሬ” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ባዘጋጀው የእውቅናና የሽልማት መርኃ ግብር ወቅት ነው። ሽልማቱን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እጅ የተቀበሉት የድርጅታችን ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ ኡርጌሳ ሽልማቱ ድርጅታችን ስራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገኘ እንደመሆኑ ድርጅታችን በትክክለኛ መንገድ ለመገኘቱ ማረጋገጫ ነው ያሉ ሲሆን ይህ ውጤት እንዲመጣ ምክንያት የሆኑ በየደረጃው ያሉ የድርጅታችን ሰራተኞችና አመራሮችን አመስግነዋል። ይህ እውቅናና ሽልማት የበለጠ እንድንተጋ የሚያደርግና ኃላፊነት የሚጥል መሆኑንም አስገንዝበዋል።
top of page
bottom of page
Comments