top of page
Search

ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ።

ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አክስዮን ማኅበር ለእንስሳት መኖ የሚሆን የገብስ ተረፈ ምርት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ለሚገኙ የድርቅ ተጋላጭ አካባቢዎች ማድረስ ችሏል። በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ያለመው ድጋፉ በፈንታሌ ወረዳ በሚገኙ 18 ቀበሌዎች ለሚገኙ አርብቶ አደሮች እንዲከፋፈል ተደርጓል።

በመተሐራ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ለማኅበረሰቡ ያስረከቡት የዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ የሕግ እና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ የኔሰው ድረስ ይህ ድጋፍ በድርቁ ምክንያት እያጋጠመ ያለውን ቀውስ በመቀነስ ረገድ ቀላል የማይባል አስተዋፅዖ ይኖረዋል በማለት ወደፊትም ድርጅቱ ከማኅበረሰቡ ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል።

በዕለቱ ድጋፉን የተረከቡት የማኅበረሰብ ተወካዮችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


26 views0 comments

Comments


bottom of page