top of page
Search

አዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ እና ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረሙ።


ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ በዋሊን ቢራ ምርቱ ከአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጋር በአጋርነት ለመስራት ለቀጣዮቹ አምስት አመታት የሚተገበር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርሟል፡፡


ይፋዊ የፊርማ ስነ-ስርዓቱ አርብ መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አመራሮች፣ የቡድን አባላት እና ደጋፊዎች እንዲሁም የስፖንሰሩ ዩናይትድ ቤቨሬጅስ አ.ማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና በርካታ የስፖርት ቤተሰቦች በተገኙበት በቤስት ዌስተርን አዲስ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን በዚህ ስምምነት መሰረት ዋሊን ቢራ በአምስት አመት ውስጥ በአይነት እና በጥሬ ገንዘብ አጠቃላይ የ60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለማድረግ ተስማምቷል፡፡


ይህ ድጋፍም በዋነኝነት የክለቡን የፋይናንስ አቅም በቀጥታ ለማሳደግ፣ የክለቡን ደጋፊዎች እና ማህበራዊ መሰረት ለማጠናከር፣ እና የክለቡን ዋና ዋና የስፖርት ልማት ፕሮጀክቶች ለመደገፍ የሚውል ይሆናል ተብሏል፡፡ ከዚህ ባሻገር ክለቡ የራሱን ገቢ የሚፈጥርበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚረዱ ተግባራትን ዋሊን ቢራ በልዩ ትኩረት የሚያግዝ ይሆናል።



68 views0 comments

Comments


bottom of page